=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸውና በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።
ቁርአን ለማንበብ ግልፅ የሆነ ልንስራራበት እና ልናስተነትንበት የሚገባ ሲሆን ለሰው ልጆች በረካ የሆነ መለኮታዊ መጽሐፍ ነው።
አሏህ ስለ ቁርአን እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 59:21})>=
{21} ይህንን ቁርአን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአሏህ ፍራቻ የተነሳ ተዋራጅ ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር። ይህችንም ምሳሌ ያስተነትኑ ዘንድ ለሰዎች እንገልፃለን።
መሬት ሚዛኑዋን እንድትጠብቅ አጥብቆ በያዛት እና ግርማሞገስን በተላበሰው ተራራ ላይ ያለው ተፅዕኖ እንኴ ውጤቱ ይህ ነው።
በሙስሊም እንደተዘገበው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-ከአሏህ ቤት የአሏህን መጽሐፍ ለመቅራትና በአንድላይ ሊያጠኑት የሚሰባሰቡ ሰዎች የሉም የመንፈስ እርጋታና ምህረት አካቧቸው ፣ መላኢካዎች ከበዋቸውና አሏህ ከነሱ ጋር ሆኖ ቢሆን እንጂ ብለዋል።
ቁርአን በራሱ ተአምር የሆነ የአሏህ ንግግር መሆኑን እናውቃለን። ይህ እምነት የእምነታችነን መሠረታዊ ክፍል ይፈጥርልናል። ከዚህ በተጨማሪም አሏህ(ሱ.ወ.ተ) በቁርአን ውስጥ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 3:190})>=
{190} በእርግጥ በሰማያትና በምድር ፍጥረት ውስጥ እንዲሁም በሌሊትና በቀን መፈራረቅ ውስጥ ለሚረዱ ሰዎች ምልክቶች አሏቸው።
ቁርአን ከኛ በላይ ባለው ሰማይ ፣ ከስራችን ባለው መሬት ፣ በዙርያችን ባሉ ዛፎች ፣ አእዋፍት ፣ ሸለቆዎች ፣ ወራጅ ውሃዎች ፣ ባህሮች እንዲሁም በፀሀይ ፣ በጨረቃ ፣ በዝናብ ፣ በከዋክብት ወ.ዘ.ተ እንድናስተነትን በሚያደርጉ አያቶች(ምልክቶች) የተሞላ ነው። ቁርአን በዙርያችን ባሉ ነገሮች ትልቅም ሆነ ትንሽ እንድናስተነትን ጌታችንን እንድናውቅና እንድናልቀው ይረዳናል።
የቁርአን ተአምር የሚገኘው በመመሪያነቱ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ቁርአን ከ1000 ዓመታት በላይ ያልተከለሰ ያልተበረዘ እንዲሁም ያልተቀየረ ነው።
ቁርአን የሰው ልጅ የፈጠራ ስራ ነው ብለው የሚያስቡትን በማስተባበል አሏህ የሰው ልጆችን እንዲህ ሲል ይፈትናቸዋል:-
=<({አል-ቁርአን 52:34})>=
{34} እውነተኞች ከሆኑ ተመሳሳይ የሆነች (አያት) እንዲያመጡ አድርጋቸው።
አንድም የሰው ልጅ ቁርአንን ወይም አያቶቹን(አንቀፆቹን) የሚመስል ምንም ነገር ማምጣት ወይም መፍጠር አልቻሉም። እንዲያውም እንኴ ወደ አሏህ (ሱ.ወ.ተ) ቃል የተጠጋ ድንቅና ያሸበረቀ ያማረ ስድንባብ አይደለም በአረብኛ በሌላ ቇንቇ እንኴ የፈጠረም ሆነ ያመጣ አንድም የለም።
የቁርአን የሰዋሰው ትክክለኛነት የቅላፄውና የድምፀ ልሳኑ ውበት እስከ ትንሳኤው ቀን ዘላቂ ሲሆን ከቁርአን ጋር የሚመሳሰልም ሆነ የሚጠጋ የቁንቇ ተዐምር አልተፈጠረም አይፈጠርም።
=<({አል-ቁርአን 4:82})>=
{82} ቁርአንን አያስተነትኑትምን? ከአሏህ ውጭ የሆነ ቢሆን ኖሮ ብዙ ቅራኔዎችን እርስበርስ የሚጋጩ ነገሮችን ባገኙበት ነበር።
ከሁሉም በላይ ከገፅ እስከ ገፅ የሚነበብ በሰው ልጆች አእምሮ እያንዳንዱ ቃል ተሸምድዶ የተቀመጠ ብቸኛው መጽሐፍ ነው።
=<({አል-ቁርአን 15:9})>=
{9} በእርግጥ ዚክሩን(ቁርአንን) ያወረድ ነው እኛነን። በእርግጥም እንጠብቀዋለን።
ቁርአን ከ1400 ዓመታት በፊት የተገለፀ ሲሆን የቁርአንም መልዕክት ታማኝና ታዛዥ በሆኑ የአሏህ ባሪያዎች እየተማሩትና እያስተማሩት ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ እዚህ ላይ ደርሷል።
በቡኻሪ እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከእናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው ብለዋል።
እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ጊዜው ሳይጨልምብን የሞትን ቅጣት ከመቅመሳችን በፊት ወደ ቁርአን ወደ ሱና እንመለስ። አሏህ (ሱ.ወ.ተ) የሂወታቸው መመሪያ ቁርአንና የሐዲስን ካደረጉት እንዲሁም ቁርአንን ለማወቅም ሆነ ለማሳዎቅ ከሚጣጣሩት መካከል ያድርገን። አሚን!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|